ነገ በአዲስ አበባ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
ነገ ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን ታላቁን የኢፍጣር መርኃ ግብር ምክንያት በማድረግ፣ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሚከተሉት መንገዶች ዝግ ይደረጋሉ፦
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን
• ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ
• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፤ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡
• ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ
• ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ
• ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ
• ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር
በተጠቀሱት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል።
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
