የበካይ ጋዝ ልቀት መጠን ለመቆጣጠር ክትትል ተጀምሯል።
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከተሽከርካሪዎች የሚወጣውን በካይ ጋዝ ልቀት መጠንን (ጭስ) ለመቆጣጠር የሚያስችል የክትትል ተግባራት መጀመሩን የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሳውቋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ፥ " ተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ ልቀት ልኬት ተደርጎለት ደረጃውን ካላሟላ በቀጠይ አሰተካክሎ እንዲመጣ የሚደረግ ሲሆን ደረጃውን ካለፈ ደግሞ የማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ማግኝት ይችለሉ " ብሏል።
ከቀናት በፊት በዚሁ የበካይ ጋዝ ልቀት ቁጥጥር ጉዳይ መግለጫ ተሰጥቶ ነበር።
መግለጫውን ሰጥተው የነበሩት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ፤ ተሽከርካሪዎች የሚለቁት የጋዝ መጠን ገደብ መቀመጡን አስንተዋል።
በተለይ ያረጁ ተሽከርካሪዎች የበካይ ጋዝ ልቀታቸውን እንዲቀንሱ ቴክኖሎጂ (ጭሱን እንዲቀንስ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ) መጠቀም እንዳለባቸው ፤ ይህን የማያደርጉ ከሆነ እንዳያሽከረክሩ እንደሚታገዱ ተናግረዋል።
በተለይ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉና ሞተራቸው ያረጀ ተሸከርካሪዎች የሚለቁት በካይ ጋዝ ከፍተኛ በመሆኑ ካላስተካከሉ እንደሚታገዱ አስታውቀዋል።
" መንግስት የነዳጅ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎችን ዜሮ ማድረግ/ሙሉ በሙሉ እንዳይኖሩ ማድረግ ሳይሆን የሚለቁትን ጋዝ ነው መገደብ የፈለገው " ሲሉ ተናግረዋል።
በመሆኑም የሚለቁት የበካይ ጋዝ መጠን ከተቀመጠው ስታንዳርድ በልጦ ክልከላ እንዳይጣልባቸው ቴክኖሎጂውን መጠቀም ወይም ወደ ታዳሽ ኃይል/ወደ ኤሌክትሪክ አልያም የተፈጥሮ ጋዝ መቀየር እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የበካይ ጋዝ ልቀጥ መጠንን ለመቆጣጠር የተዘጋጀውን ስታንዳርድ ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ሲሆን ሁሉንም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ይመለከታል ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከበካይ ጋዝ ልቀት ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች ፥ አንድ ተሽከርካሪ " ደረጃ አላሟላም " የሚባለው መጠኑ በቁጥር ስንት ሲያስመዘግብ እንደሆነ በግልጽና በይፋ ለህዝብ ካልተገለጸ ፤ በሚዲያም የማሳወቅ ስራ በስፋት ካልተሰራ ሁኔታው ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚያጋልጥ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።
#afromekina
Loading content...
