ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ነዳጅን በዝቅተኛ ዋጋ የምትሸጥ ኢትዮጵያ ናት ጠ/ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
ባለፈዉ አንድ አመት ተኩል የነዳጅ ገበያ ዋጋን አትዮጵያ የቀየረችዉ ሰባት ጊዜ መሆኑ ተነግሯል።
ይህም ኢትዮጵያ ነዳጅ ሳታመርትና እንደሌሎች ሀገራት በየጊዜዉ ሳትጨምር መሆኑ ተገልጿል፡፡
ነዳጅ ከ60 እስከ 90 ዶላር ከፍ ማለቱን እና ለዚህም እንደምክንያት የተነሳዉ በመካከለኛዉ ምስራቅ የነበረዉ ግጭትና በቀይ ባህርና በኢራን ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2018 በጀት ዓመት በ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በሚያቀርቡ ወቅት ነዉ ይህን ያሉት።
ለዚህም በየጊዜዉ የሚታየዉ ሰልፍ ስግብግብ ነጋዴዎች ከዚህ ድጎማ ለመቀራመት የሚያደርጉትን ጥረት በበቂ መቋጣጠር ባለመቻሉ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አሁን በየቦታዉ አዳዲስ ማደያዎችን እንደ ፋሽን የሚከፈቱት ለህዝብ በማሰብ ሳይሆን ከድጎማዉ ለመጠቀም እንደሆነ ተናግረዋል።
#afromekina
Loading content...
