የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ 26 የኤሌክትሪክ መኪኖችን ተረከበ
ርክክቡን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍሰሃ ይታገሱ እና የአቶ በላይነህ ክንዴ በተገኙበት ተከናውኗል።
አቶ ፍሰሃ እንደገለጹት፣ ይህ ግዥ ኮርፖሬሽኑ አካባቢን ከብክለት ለመከላከልና ወጪን ለመቀነስ የጀመረው ጥረት አካል ነው። በአሁኑ ወቅት የኮርፖሬሽኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቁጥር ከ50 በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም አጠቃላይ የተሽከርካሪ ድርሻውን 30 በመቶ ያደርሰዋል።
አቶ በላይነህ ክንዴ በበኩላቸው መኪኖቹ አስተማማኝ የጥገና ማዕከልና መለዋወጫ እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
ኮርፖሬሽኑ በሂደት የነዳጅ መኪኖችን በኤሌክትሪክ ለመተካት እየሰራ ሲሆን፣ ይህም ለሰራተኞች ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠቱም ባለፈ ለነዳጅና ለኪራይ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ ታምኖበታል።
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
