26 የከተማ አውቶቡሶች በተፈጥሮ ጋዝ መሥራት ጀመሩ!
400 አዳዲስ አውቶቡሶችም ወደ ሀገር ይገባሉተባለ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ተመልሰው፣ ዛሬ የመጀመሪያዎቹ 26 የከተማ አውቶቡሶች ከነዳጅ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ተቀይረው ሥራ መጀመራቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ እርምጃው በነዳጅ ግዢ ላይ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለመቆጠብና የሕዝብ ትራንስፖርት የሥራ ማስኬጃ ወጪን ለመቀነስ እንደሚረዳ ጠቁመዋል። በዚህም የዜጎችን የጉዞ ታሪፍ በግማሽ ለማቃለል እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ባለፉት ወራት የከተማ አውቶቡሶቹን ወደ ተፈጥሮ ጋዝ የመቀየር፣ ጋዙን ከሚመረትበት ስፍራ ወደ አዲስ አበባ የማጓጓዝ፣ የጋዝ ማደያዎችን የማዘጋጀት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውቀዋል።
ይህም የሀገር ውስጥ አቅምን በመጠቀም የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማምጣት የተደረገ ጥረት መሆኑን ጠቅሰዋል።
በቀጣይም በነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስና የሀገር ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀምን ለማስፋት 400 አዳዲስ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ አውቶቡሶች በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
#afromekina
Loading content...
