በዓለማችን እጅግ ቀጭኗ መኪና እውን ሆነች
ጣሊያናዊው መሐንዲስና ዩቲዩበሪ ካርማጌዶን (አንድሪያ ሞቺያ) በዓለማችን ላይ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ በጣም ቀጭን መኪናን ሰርቶ ለዓለም አሳይቷል። ይህች "ፊያት ፓንዳ" (Fiat Panda) የተሰኘችው መኪና የጎን ስፋቷ 50 ሴንቲ ሜትር (19.6 ኢንች) ብቻ ሲሆን፣ በማንኛውም ጠባብ መንገድ ውስጥ በቀላሉ የመሹለክ ብቃት አላት።
አንድሪያ ይህን አስገራሚ ውጤት ለማምጣት አሮጌውን የፊያት ፓንዳ 4x4 መኪና ለሁለት በመሰንጠቅ፣ ከመሠረቱ (Chassis) እስከ መሪውና ፍሬኑ ድረስ ያለውን የሜካኒካል ክፍል በድጋሚ በመገንባት የአንድ ሰው መቀመጫ ብቻ ያላት ድንቅ ፈጠራ አድርጓታል።
መኪናዋ እንደማንኛውም ተሽከርካሪ ትነዳለች፣ ትቆማለች፣ እንዲሁም ትታጠፋለች፤ ልዩነቷ ግን ለተሳፋሪ የሚሆን ስፍራ አለመኖሩ ብቻ ነው።
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
