ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኤሌክትሪክ
ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡ ተገለፀ
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ለመንግሥት ሚዲያ እንደገለጹት፤ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሰፊ የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
አዳዲስ ተሽከርካሪዎችን ከማስገባት ባለፈ፣ ነባርና ዕድሜ ጠገብ የሆኑ የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የመቀየር ሥራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም፤ ተሽከርካሪ ወደ ሀገር በማስገባት የተሰማሩ አስመጪ ነጋዴዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ኢሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የነዳጅ ተሽከርካሪ በማስመጣትና በመገጣጠም ይሰሩ የነበሩ ተቋማት ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ ትኩረት አድርገው እንደሰሩ እየተደረገ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡
ቀደም ሲል ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ የጥራት ክፍተቶችን ለመቅረፍም፣ የሀገሪቱን የመልክዓ ምድርና የአየር ንብረት ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገቡ ጥብቅ መመዘኛዎች በመዘርጋት ላይ ናቸው ብለዋል።
#afromekina
Loading content...
