ኢትዮጵያ ከመኪናቸው ጭስ ማውጫ ብዙ በካይ ጋዝ የሚለቁ መኪኖችን ከመንገድ ልታግድ ነው ተባለ
በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የሚለቁትን በካይ ጋዝ ለመቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ እንዲገጥሙ ሊደረግ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከዕፅዋት የሚዘጋጅ የአውሮፕላን ነዳጅ ለመጠቀም የሚያስችል ዘላቂ የአቪዬሽን ነዳጅ ላይ የተሠራ የአዋጭነት ጥናት ሪፖርት ሲያቀርብ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ ፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች የሚለቁት በካይ ጋዝ ምን ያህል መሆን እንዳለበት የሚወስን ስታንዳርድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ስታንዳርዱን ያዘጋጀው ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር መሆኑንና አሽከርካሪዎች በተዘጋጀው ስታንዳርድ መሠረት የማይጠቀሙ ከሆነ እንደሚታገዱ፣ በተለይም ለረዥም ጊዜ ያገለገሉና ሞተራቸው ያረጀ ተሽከርካሪዎች የሚለቁት በካይ ጋዝ ከፍተኛ በመሆኑ ካላስተካከሉ እንደሚታገዱ አስታውቀዋል፡፡
#afromekina
Loading content...
