የባለስልጣኑን ምዘና በማያልፉ የቦሎ አገልግሎት ሰጪ የተሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ ውክልና እንደሚነጠቅ ተገለጸ
በአሽከርካሪ እና ተሸከርካሪ ባለስልጣን የሚከናወነውን ምዘና በማያልፉ የቦሎ አገልግሎት በሚሰጡ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ ውክልና እስከ መንጠቅ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጻል፡፡
ለተሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚከናወን ለአሐዱ የተናገሩት፤ የባለስልጣኑ የተሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግሥት አሰፋ የቦሎ አገልግሎት በሚሰጡ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ በባለስልጣኑ በሚከናወነው ምዘና ክፍተት ከተገኘባቸው ውክልና እስከ መንጠቅ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸል፡፡
በባለሥልጣኑ የተሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግሥት አሰፋ ገለጻ በአሽከርካሪ እና ተሸከርካሪ ባለስልጣን በተሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ በተከናወነ የምዘና ግምገማ ክፍተት በሚገኝባቸው ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በባለፈው ዓመት በተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ በተከናወነ ምዘና የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምዘና ባላሟሉ እና ክፍተት በተገኘባቸው የተሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ውክልና የመንጠቅ እርምጃ እንደተወሰደ አውስተዋል፡፡
የተሸከርካሪ ባለንበረቶች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የተሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ የቦሎ አገልግትን እንዲያገኙ ለማስቻል እቅድ ስለመያዙ ጠቁመዋል፡፡
#afromekina
Loading content...
