የተሽከርካሪ አስመጪዎችን አግደናል
‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሟላ የተሽከርካሪ መሠረታዊ ሰነዶችን አሟልተው ሳያስረክቡ፣ የተሽከርካሪ ገዥዎችን ወደ ተቋሙ የሚልኩ እንዲሁም ጉዳይ አስፈፃሚን በመመደብ ከተገልጋይ ተጨማሪ ክፍያን የሚቀበሉ አስመጪዎችን ከአሁን በኋላ በተቋሙ አገልግሎት እንዳያገኙ አገደ።
" ሁሉም የተሽከርካሪ አስመጪዎች፣ ለገዥዎች የተሟላ የተሽከርካሪ መሠረታዊ ሰነዶችን በመስጠት፣ ገዢዎች ወደ ተቋሟችን መጥተው ያለ እናተ ጉዳይ አስፈፃሚ፣ ያለ እንግልት እና ውጣ ውረድ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ መረጃ እንድትሰጡ " ሲል በጥብቅ አሳስቧል።
#afromekina
Loading content...
