በኢትዮጵያ በ2033 የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ከ40 በመቶ ወደ 80በመቶ ለማሳደግ ታቅዷል
ኢንጂነር ባህሩ ኦልጂራ እንደተናገሩት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ተጠቃሚዎችን ለማበራከት ከተዘጋጀው የታክስ ማበረታቻ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ መንግስት ከጥር 2017 ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ መኪና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ሙሉ በሙሉ ማገዱን አስታውሰው እነዚህ ማበረታቻዎች ከውጪ የሚገቡትን ቀረጥ እና ለግል ቤት ቻርጀሮች ነፃ ማድረግ፣ ግለሰቦች እና የንግድ ድርጅቶች በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያበረታታ መሆኑም ተናግረዋል።
በዚህም እንደሀገር በ2033 የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ቁጥር ከ40 በመቶ ወደ 80በመቶ ለማሳደግ ትልቅ እቅድ በመያዝ የትራንስፖርት ዘርፉን ለመለወጥ መመሪዎች በማዘጋጀት እቅድ ተይዛል ተብላል።
የሀገሪቱን ቀጣይ የትራንስፖርት ዘርፉ በሚመራበት ስትራቴጂ ጋር በተያያዘ በነዳጅ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን ለመቀነስ የተያዘውን ዕቅድ ውይይት እየተደረገበት መሆንንም ለማወቅ ችለናል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከጥር 2017 ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ መኪና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ሙሉ በሙሉ መወሰኑ ይታወሳል።
#afromekina
Loading content...
