የጀርመኑ ቮልክስዋገን በአሜሪካን ቀረጥ ምክንያት በ2025 ከፍተኛ ኪሳራ አጋጠመው
ግዙፉ የመኪና አምራች ቮልክስዋገን በ2025 በሦስተኛው ሩብ ዓመት 1.24 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ኪሳራ ሪፖርት ማድረጉን የጀርመን መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
በዚህም ኩባንያው በአምስት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሩብ ዓመት ኪሳራ ያጋጠመው መሆኑን ተጠቁሟል።
ከፖርሼ የምርት ስትራቴጂ ማስተካከያ በተጨማሪ፣ ለተመዘገበው ዝቅተኛ አፈጻጸም ከፊሉ ከፍ ያሉ የአሜሪካ ቀረጦች መሆናቸውን የቮልክስዋገን የፋይናንስ እና ኦፕሬሽን ኃላፊ አርኖ አንትሊትዝ ገልጸዋል።
በአጠቃላይ፣ አሜሪካ በአውሮፓ ሕብረት ላይ የጣለቻቸው አዳዲስ ቀረጦች ቮልክስዋገንን በዓመት 5.7 ቢሊዮን ዶላር ያህል እንደሚያሳጡት ዘገባው አመልክቷል።
#afromekina
Loading content...
