ኢትዮጵያ የነዳጅ ማከማቻዋን ወደ ጅቡቲ ዳመርጆግ ወደብ ለማዘዋወር እያጤነች ነው ተባለ
👉 ይህም የሀገር ውስጥ የነዳጅ ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ፣ አሁን ያሉት ማከማቻዎች በመሙላታቸው እና ነዳጅ ለሚያመጡ መርከቦች ከሚከፈለው ከፍተኛ የመዘግየት ክፍያ ጋር ተያይዞ የመጣ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
🇪🇹🇩🇯 የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ ከጅቡቲ የወደቦችና ነፃ ቀጣና ባለሥልጣን ሰብሳቢ አቡበከር ኦማር ሀዲ እና ከጅቡቲ አቻቸው ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ የዳመርጆግ የነዳጅ ተርሚናሎች ከነጋድ የባቡር ጣቢያ ጋር እንዲገናኙ ጥያቄ አቅርበዋል።
🏗 የዳመርጆግ ተርሚናል በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ከምትጠቀምበት የሆራይዘን ዴፖ በተሻለ ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን የማስተናገድ አቅም እና ሰፊ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ አለው።
#afromekina
Loading content...
