የአዳዲስ ነዳጅ ማደያዎች ግንባታ ላልተወሰነ ጊዜ መከልከሉ ተገለፀ
ከመንግሥት በተሰጠ አቅጣጭ መሠረት የአዳዲስ ነዳጅ ማደያዎች ግንባታ ላልተወሰነ ጊዜ መከልከሉን፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
ባለሥልጣኑ ይህንን ያስታወቀው የነዳጅ ውጤቶች የገበያ ድርሻ ቀመር ክለሳ ጥናትና የነዳጅ ውጤቶች የሥርጭት ቀመር የአሠራር ሥርዓት መመርያ የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች በተገኙበት፣ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት በተደረገበት መድረክ ላይ ነው፡፡
በዚሁ ወቅት የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲባራ ፉፋ ማደያዎችን ጉዳይ በተመለከተ ሲያስረዱ፣ "አዳዲስ ኩባንያዎች ባሉበት ይቆያሉ" ብለዋል።
"ከተወሰነላቸው በጣት ከሚቆጠሩ ግንባታዎች ውጪ የግንባታ ፈቃድ መስጠት አዲስ የማስጀመር ሒደት ባለበት እንዲቆም መንግሥት ወስኗል" ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ አክለውም ያሉትን በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል።
የክልል አመራሮችም ነዳጅን ከመቆጣጠር ሒደት እጃቸውን እንዲያወጡ መንግሥት ግልጽ መመርያ መስጠቱን ተናግረዋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በአራት መሥፈርቶች ማደያ የሌላቸው፣ ከፍተኛ መጨናነቅ ያለባቸው፣ በኮሪደር ልማት የፈረሱና ውስን ማደያዎች ያላቸው በተለይ ደግሞ ኮንትሮባንድ የሚበዛባቸው አካባቢዎች ያልሆኑ ተብሎ በኮሚቴ በዝርዝር ታይቶና ተለይቶ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከፈቀዳቸው ዘጠኝ ያህል ማደያዎች ግንባታዎች ውጪ ጉዳዩ ዝግ ነው ብለዋል፡፡
#afromekina
Loading content...
