ኢትዮጵያ በ2022 ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከ2.7 ቴራ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል እንደሚያስፈልጋት ጥናት አመላከተ
🔍 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ተፅዕኖ በተቋሙ የግሪድ ሲስተም ላይ በሚል ርዕስ ያስጠናውን ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡
🚘🔋በሀገሪቱ እያደገ የመጣውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቁጥር ተከትሎ በ2017 ዓ.ም የነበረው 370 ጊጋ ዋት ሰዓት የኃይል ፍላጎት በ2022 ዓ.ም ወደ 2.7 ቴራ ዋት ሰዓት እንደሚያድግ በሰነዱ ተመላክቷል፡፡
👉 የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ስትራቴጂክ እቅድን መረት በማድረግ የተከናወነው ጥናት፤ ከ2017-2022 ዓ.ም ያለውን ጊዜ የኃይል አጠቃቀም የሚዳስስ መሆኑን የጥናቱ ቡድን መሪ ኢንጅነር ሀብታሙ አበበ ገልፀዋል፡፡
🚍 የኤሌክትሪክ አውቶብሶች በኃይል ፍጆታ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ ተብሏል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር በ2030 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ለማድረስ እንዳቀደ መግለፁ የሚታወስ ነው፡፡
#afromekina
Loading content...
