የነዳጅ ዋጋ ወደ 200 ዶላር ሊያሻቅብ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀች
የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት ከቀጠለ፣ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የኢኮኖሚ ማዕከላት ላይ የአፀፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጄኔራል ኢብራሂም ጃባሪ እንደገለጹት፣ ጥቃቱ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋን ከቁጥጥር ውጭ ያደርገዋል።
ጄኔራሉ አክለውም፣ “ጠላት ዋና ዋና ተቋሞቻችንን ካጠቃ፣ እኛም በክልሉ ያሉ የኢኮኖሚ ማዕከላትን እናጠቃለን” ብለዋል።
ኢራን የሆርሙዝ የባህር ስርጥን እንደዘጋችና በአሁኑ ወቅት 80 ዶላር አካባቢ ያለው የነዳጅ ዋጋ በቅርቡ 200 ዶላር እንደሚደርስ የኢራን የዜና ወኪል ISNA ዘግቧል።
የሆርሙዝ የባህር ስርጥ ለዓለም የነዳጅ ንግድ ወሳኝ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፉ የነዳጅ ፍላጎት 20 በመቶው በዚህ መስመር ያልፋል።
በተጨማሪም የኳታር እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የተፈጥሮ ጋዝ ኤክስፖርት የሚከናወነው በዚህ ስርጥ በኩል ነው።
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
