ሊቢያ ከአሜሪካና ከፈረንሳይ ኢነርጂ ኩባንያዎች ጋር የ20 ቢ. ዶላር የነዳጅ ኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራረመች
ሊቢያ ከአሜሪካና ከፈረንሳይ ኢነርጂ ኩባንያዎች ጋር የ20 ቢሊየን ዶላር የ25 አመት ታሪካዊ የነዳጅ ኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሟን ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ዘግቧል፡፡
ቶታል ኢነርጂስ እና ኮንኮፊሊፕስ የተሳተፉበት ስምምነቱ፣ የሊቢያን የነዳጅ መሰረተ ልማት በማዘመን በቀን 850,000 በርሜል ምርትን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
ይህም ሊቢያ የአፍሪካ ቀዳሚ የነዳጅ ዘይት አምራች የሆነችውን ናይጄሪያን እንድትገዳደር ሊያደርጋት ይችላል ተብሏል፤ ምንም እንኳን ተግዳሮቶች ቢኖሩትም፡፡
የሊቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስምምነቱ ከፍተኛ የገቢ አቅም በመፍጠርና ከዓለም አቀፍ የኢነርጂ አጋሮች ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ያለውን ፋይዳ አጉልተው ተናግረዋል፡፡
#afromekina