ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ 2ኛውን የኢትዮ- ግሪን ሞቢሊቲ ሳምንት 2025 በይፋ መርቀው ከፈቱ
ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ 2ኛውን የኢትዮ- ግሪን ሞቢሊቲ ሳምንት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ መክፈቻ ንግግራቸው የአየር ብክለትን ለመቀነስ ተግባር ተኮር እንቅስቃሴ አስፈላጊ መሆኑን ያነሱ ሲሆን በዚህ ረገድ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አበረታች ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የአየር ብክለት ለመቀነስ የሚሰራውን ስራ ለመደገፍ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ በበኩላቸው የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ በታሪካዊ ሽግግር ላይ መሆኑን በመግለፅ የኢትዮ- ግሪን ሞቢቲ ሳምንት 2025 ዓላማ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር፣ ባለሃብቶች በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማበረታታት እና ዘርፉን ለማዘመን የቴክኖሎጂ ትስስር ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
መርሃ-ግብሩ ከታህሳስ 18 እስከ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም በአውደ-ርዕይ፣ እግዝብሽን እና የፓናል ውይይት ለተከታታይ አምስት ቀናት በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬክሽን ማዕከል የሚካሄድ ይሆናል።
የኢትዮ- ግሪን ሞቢሊቲ ሳምንት 2025 ከታህሳስ 18-22/2018 ለጎብኚዎች ከፍት መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ ክቡር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁሞ የሚኒስቴር መ/ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
#afromekina
Loading content...
