ፖላንድ የቻይና ምርት የሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ እገዳ ጥላለች።
የፖላንድ መንግስት በሀገሪቱ በሚገኙ ወታደራዊ ይዞታዎች እና ሚስጥራዊ ስፍራዎች የቻይና ሰራሽ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ጥብቅ እገዳ መጣሉን አስታውቋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው ዘመናዊ የቻይና መኪናዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ካሜራዎች፣ ሴንሰሮች እና የድምጽ መቅጃዎች የተገጠሙላቸው በመሆናቸው፣ ወታደራዊ ምስጢሮችን ሊሰበስቡ ይችላሉ የሚል ስጋት በፖላንድ ጦር ዘንድ በመፈጠሩ ነው።
የፖላንድ ወታደራዊ ደህንነት ተቋም ተሽከርካሪዎቹ የሰበሰቡትን መረጃ በዲጂታል መንገድ ወደ አምራች ኩባንያዎቹ ወይም ለቻይና መንግስት የደህንነት ተቋማት ሊያስተላልፉ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬም ገብቶታል።
ቤጂንግ የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአለምአቀፍ የመረጃ ደህንነት ህጎችን አክብረው ነው የሚሰሩት ስትል ምላሽ የሰጠች ሲሆን ውሳኔውን የብሄራዊ ደኅንነትን ሰበብ ያደረገ በንግድ ላይ የሚደረግ አላስፈላጊ ጫና ነው ስትል ገልጻዋለች።
#afromekina
Loading content...
