የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት የሹፌሮቻቸውን የማሽከርከር አቅም ለማሳደግ ሹፌሮች ስኪል አፕ እንዲያደርጉ ማድረግ አለባቸው ተባለ
" የተሽከርካሪውን ደህንነት ሳያረጋግጥ ሰው እንደሚገድል እያወቀ ለትራንስፖርት እያሰማራ በተሽከርካሪው ለሚደርሰው የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ተጠያቂው ባለቤቱ ነው " - ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር
የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን በመንገድ ደህንነት ላይ አስገዳጅ በመሆን የፀደቁ ደረጃዎችን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅ የወርክ ሾፕ መርሃግብር አካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርሆ ሀሰን " የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት የሹፌሮቻቸውን የማሽከርከር አቅም ለማሳደግ ሹፌሮች ስኪል አፕ እንዲያደርጉ ማድረግ አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ በርሆ ሀሰን በዝርዝር ምን አሉ ?
" በየአመቱ በትራፊክ አደጋ 4 ቢሊዮን ብር ይወድማል፣ ከ3 እስከ 4 ሺህ ዜጎችን እያጣን ነው፣ ከባድ የአካል ጉዳቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ ናቸው፣ ይህ የሚያሳየው አሁንም ያልቀረፍናቸው ሲሪየስ የሆኑ ችግሮች እንዳሉ ነው፣ ባሉን ውስን ስቶክ ከፍተኛ የሆነ ሞት እየተመዘገበ ነው፣ በአመት አንድ ትልቅ ሜጋ ፕሮጀክት መገንባት የምንችልበት ንብረትም እየወደመ ነው።
ለትራፊክ አደጋዎች መንስኤያቸው ምንድን ነው ? ሲባል የአሽከርካሪዎች የስልጠና ሂደት፣ ባህሪ፣ አመለካከት ፣ ወሳኝ የስራ ላይ ስልጠና እና አጠቃላይ የስልጠና ማዕቀፋችን ያለበት ማነቆና ጉደለት ነው።
አብዛኛው የስልጠና ተቋማት በቢዝነስ ሃሳብ (ትርፍ እና ኪሳራ) የሚመራ ነው። ይህ የሚያሳየው ኃላፊነት በተሰማው መንገድ እየመራን አለመሆኑን ነው።
የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት በአግባቡ ተሽከርካሪዎችን እየመረመሩ አይደለም፣ ባለቤቶችም ወደ መንገድ ሲወጡ መኪናቸውን ፈትሸው ነወይ ? ሲባል ከፍተኛ የሆነ ክፍተት አለ፣ ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት የሚቀርበው የስፒድ ፓርት መወደድ ነው፣ ይህን ግን ቻል አድርገን ነበር፣ ነገር ግን የሰው ህይወትን መታደግ አልቻልንም።
የሰው ህይወት እየቀጠፉ ያሉት የሜንቴናንስ ችግር ያለባቸው እና ችግር እንዳለባቸው እያወቅን የምናሰማራቸው ተሽከርካሪዎች ናቸው። ' ይችን ትሪፕ ደርሰህ ና ' የሚል ባለንብረት፣ የተቋም ኃላፊ እና የስምሪት ኋላፊ ብዙ ነው፣ ይህ የመንግስት ተቋማትንም ይጨምራል።
ጎማቸው አገልገሎት መስጠት የማይችል የሆኑ ፣ ብዙ የሜንቴናንስ ችግር ያለበት፣ የፍሬን ችግር እንዳለው እያወቁ የሚያሰማሯቸው ተሽከርካሪዎች ዋጋ እያሰከፈሉን ነው፣ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የተፈጠሩት የቴክኒክ ምርመራ ተቋማት አብዛኛው በሃሰት ወረቀት የሚያትሙ እና የሚሸጡ በመሆናቸው ነው፣ በተቋቋሙበት አዋጅ እና ደንብ እየሰሩ አለመሆኑንም በፍተሻ አረጋግጠናል።
የት ጋር ችግር እንዳለ እና የትኞቹ ተቋማት እንደሆኑ ለይተን ጨርሰናል፣ ቦሎ የለጠፈው ካንተ ተቋም ነው፣ ምንም ህይወት ለሌለው መኪና እንደት ቦሎ ትሰጣለህ ? ብለን ስንጠይቃቸው ' እኔ ብከለክለው ከጎኔ ያለው ተቋም ይሰጠዋል፣ እኔ ደግሞ ደንበኛዬን ማጣት አልፈልግም ብየ ነው ' የሚል ምላሽ ነው የሚሰጡት። ከዚህ በኃላ ግን እርምጃ እንወስዳለን፣ በይቅርታ የሚታለፍ የለም፣ እስከዚህ ድረስ ወርደን እየሰራን ነው።
በራሱ ተሽከርካሪ ላይ መስራት ያለበትን ባመስራቱ ለሚጠፋ የሰው ህይወት ባለ ንብረቱ ተጠያቂ ነው፣ ሰው እንደሚገድል እያወቀ ለትራንስፖርት እያሰማራ በተሽከርካሪው ለሚደርሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት ተጠያቂው ባለቤቱ ነው።
እንደእስካሁኑ ለፈጣሪ የምንተወው ስራ አይደለም፣ አደጋ ያደረሰውን ተሽከርካሪ ተከታትለን ሹፌሩን እና ባለንብረቱን ተጠያቂ የሚያደርግ ስርአት እየዘረጋን ነው።
ባለንብረቶች በተቻላቸው መጠን ተሽከርካሪዎች አደጋ እንዳያደርሱ ግድ ዎርዝ እንዲሆኑ መስራት አለባቸው። በየጊዜው ሹፌሮቻቸው ስኪል አፕ እንዲያደርጉ በየጊዜው ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ የባለንብረቶች ኃላፊነት ጭምር ነው፣ይህ የመንግስት እና የግል ተቋማትን ይጨምራል " ሲሉ ተናግረዋል።
#afromekina via #TikvahEthiopia
Loading content...
