በነዳጅ ስርጭት ላይ አዲስ አሰራር ተዘረጋ!
የኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ ከነዳጅ ስርጭት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እና ህገ-ወጥነትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች የገበያ ድርሻ ድልድል ይፋ አደረገ።
📌 ለውጡ ለምን አስፈለገ?
ባለስልጣኑ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው፣ ከሚያዚያ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረው አሰራር፦
👉በነዳጅ ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ሲነሳበት የቆየ በመሆኑ፤
👉ለህገ-ወጥ አሰራር እና በማደያዎች መካከል የጭነት አድሎአዊ አሠራር እንዲፈጠር መንገድ በመክፈቱ፤
👉ለነዳጅ ስርጭትና ቁጥጥር ስራ አመቺ ባለመሆኑ አዲሱ አሰራር አስፈላጊ ሆኗል ብሏል።
📊 አዲሱ የድልድል መስፈርት ምን ምን ያካትታል?
አዲሱ የገበያ ድርሻ ዝግጅት በዘፈቀደ ሳይሆን የሚከተሉትን ነጥቦች ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፦
👉የየአካባቢው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ፤
👉የማደያዎች ብዛትና የነዳጅ መያዝ አቅም (Storage capacity)፤
👉የዲስፔንሰር (መቅጃ) ብዛት፤
👉የኮታ አካባቢዎችን ሳይጨምር፣ ከኮታ ውጭ ያሉ ማደያዎችንና ቀጥታ ተጠቃሚዎችን ያካተተ ነው።
📅 ተግባራዊ የሚሆንበት ጊዜ
ይህ አዲስ የገበያ ድርሻ ድልድል ከዛሬ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል።
⚠️ ጥብቅ ማሳሰቢያ
የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ለእያንዳንዱ ማደያ በተቀመጠው መስፈርትና በተደለደለው መጠን መሠረት የጭነት ፕሮግራም በማውጣት እንዲያሰራጩ ባለስልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።
ይህ አሰራር በነዳጅ ማደያዎች አካባቢ የሚታየውን ሰልፍና የመደበቅ ተግባር ይገታል ተብሎ ይጠበቃል።
#afromekina
Loading content...
