ዳንጎቴ ለናይጄሪያ በየወሩ 1.5 ቢ. ሊትር
ቤንዚን ለማቅረብ ቃል ገባ
ኩባንያው ከታህሳስ 2025 እስከ ጥር 2026 በቀን 50 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ እንደሚያቀርብ፤ ከየካቲት 2026 ጀምሮ ደግሞ አቅርቦቱን በቀን ወደ 57 ሚሊዮን ሊትር እንደሚያሳድግ በመግለጫው አስታውቋል።
ሙሉ ግልጽነኝነትን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን የገለጸው ዳንጎቴ፤ የዕለት ምርቱንና የክምችት መጠኑን በኦንላይንና በህትመት ሚዲያዎች ተደራሽ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ብሏል።
በተጨማሪም የናይጄሪያ የመካከለኛ ዘርፍ የነዳጅ ቁጥጥር ባለሥልጣን ጥሬ እቃዎችን፣ ግብዓቶችንና ውህድ ክፍሎችን ያለእንቅፋት ማስገባቱን እንዲደግፍ ጠይቋል።
"የናይጄሪያን የሀገር ውስጥ ነዳጅ ደህንነትና ሰፊ አቅርቦት ለማረጋገጥ የተለመደ ትኩረትና ድጋፋችሁን እናደንቃለን። የ 'ናይጄሪያ ቅድሚያ' ፖሊሲ ለሁሉም ናይጄሪያውያን ጥቅም እንዲሠራ እንጠይቃለን" ሲልም በመግለጫው ገልጿል።
#afromekina
Loading content...
