#እንድታውቁት
ከቦሌ ብራስ- በኤድናሞል ወደ አትላስ ሆቴል የሚወስደው ኮሪደር በግንባታ ምክንያት ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
በሥፍራው የሚካሄደውን የኮሪደር ልማት በፍጥነት ለማጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች በከፍተኛ ትጋት እየሰራ መሆኑን እየገለፀ፣ በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት በአትላስ መብራትና አካባቢው በሚከናወነው የግንባታ ሥራ ምክንያት፤ ቅዳሜ ህዳር 13 እና እሁድ ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቦሌ ሩዋንዳ አቅጣጫ ወደ ውሃ ልማትና ተቃራኒ አቅጣጫ የሚወስደው መንገድ ለትራፊክ ዝግ የሚደረግ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለግንባታው መፋጠን እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
#afromekina
