" መርሃ ግብር የወጣላቸው ቦቴዎች ብቻ ናቸው ወደ ጂቡቲ እንዲሄዱ (ነዳጅ እንዲጭኑ)የሚደረጉት ከመርሃ ግብራቸው ውጪ ወደዛ መሄድ አይፈቀድም " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን
ከዚህ ቀደም የነዳጅ ኩባንያዎች ምን ያህል ነዳጅ ማቅረብ እንዳለባቸው ሳይታወቅና እያንዳንዱ ኩባንያ የየራሱን መጠን ሲያቀርብ የነበረውን አሰራር የሚቀይር አዲስ የነዳጅ ስርጭት መመሪያ በይፋ ስራ መጀመሩ ይታወቃል።
" የተከለሰው የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች የገበያ ድርሻ ድልድል " አሰራር ኩባንያዎች ያላቸውን አቅም መሰረት ባደረገ ቀመር ነዳጅ እንዲያሰራጩ የሚያስገድድ ነው።
አዲሱ አሰራር ያመጣቸዋል ተብለው የሚጠበቁ ለውጦች ምንድን ናቸው ?
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት(ዶ/ር) ምን አሉ ?
" ይህ አሰራር በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች የሚታየውን የነዳጅ ሰልፍና እጥረት ይፈታል።
አሰራሩ በአንድ ማደያ ውስጥ በርካታ ዲስፔንሰሮች(የነዳጅ መቅጃ ማሽኖች) ያላቸውንና ጥቂት ዲስፔንሰሮች ያላቸውን ማደያዎች በቁጥር ብቻ ሳይሆን በአቅም እንዲለዩ የሚያደርግ ነው።
በአዲስ አበባ በዙሪያው ባሉ ከተሞች ነዳጅ ሲጠፋ ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ጫና ይፈጥሩ ነበር፣ አዲሱ ስሌት ግን በሁሉም አካባቢዎች ነዳጅ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲኖር ያደርጋል።
ቀደም ሲል አንዳንድ ኩባንያዎች ቁጥጥር ወደሌለባቸው የድንበር አካባቢዎች ነዳጅ በዘፈቀደ በመጫን በተሻለ ዋጋ ይሸጡ ነበር አሁን ግን እያንዳንዱ ኩባንያ የሚጭነው መጠንና የሚሄድበት አካባቢ አስቀድሞ ስለሚታወቅ ከዛ ውጪ መጫን አይችሉም።
ኩባንያዎች ከወር በፊት ለእያንዳንዱ ማደያ የጭነት መርሐግብር (Schedule) የሚያወጡ ሲሆን፣ ይህ መርሐግብር ለነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ቀርቦ የጭነት ፕላን ይወጣለታል።
በዚህም መሰረት በሺዎች የሚቆጠሩ ቦቴዎች ጂቡቲ ላይ ሄደው ወረፋ የሚጠብቁበት አሰራር ቀርቶ፣ መርሐግብር የተያዘላቸው ቦቴዎች ብቻ ወደ ጂቡቲ እንዲሄዱ ይደረጋል።
ማደያዎች ለኩባንያዎች ገንዘብ ከፍለው ለረጅም ጊዜ 'ወረፋ ጠብቁ' የሚባሉበትና ኩባንያዎች በማደያዎች ገንዘብ የሚነግዱበት አሰራር እንዲቀንስ ያደርጋል።
እያንዳንዱ ባለማደያ መቼ ነዳጅ እንደሚጫንለት ስለሚያውቅ የክፍያ ጊዜውንም አስቀድሞ ለማቀድ ያስችለዋል።
የአሰራሩ ዋና ዓላማ ሀገሪቱ ያላትን አቅም በመጠቀም መሰረት ያለው የነዳጅ ስርጭት እንዲኖር ማድረግ ነው " ብለዋል።
Credit to @tikvahethiopia
#afromekina
Loading content...
