በቻይና ከወራት በፊት ክፍት የተደረገ ድልድይ ፈርሷል።
በደቡብ ምዕራብ ቻይና የሚገኘውና 758 ሜትር የሚረዝመው ድልድይ ቻይናን ከቲቤት ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ግንባታውም ከወር በፊት ነበር የተጠናቀቀው።
በተራራማ አካባቢ የተሰራው ድልድይ ከባድ ዝናብ ከዘነበና የመሬት መንሸራተት ካጋጠመ በኋላ በከፊል መፍረሱ ተነግሯል።
ድልድዩ ለትራፊክ በአካባቢው የነበረውን ሁኔታ ተከትሎ ዝግ ቢደረግም በፈረሰበት ወቅት አንድ መኪና ሲሄድ እንደነበር ነገር ግን ሹፌሩ ስለመትረፉ ተነግሯል።
በአካባቢው ድልድዩ ከመፍረሱ በፊት መሬት መሰነጣጠቅና የተራራ እንቅስቃሴ ማጋጠሙም ተነግሯል።
ቻይና የድልድዩን መፍረስ ተከትሎም ምርመራ መጀመሯ ተሰምቷል።
#afromekina
Loading content...
