በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ፈጣን መስመር ግንባታ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ተገለፀ
🚍 በመዲናዋ የመጀመሪያ የሆነውና ከፒያሳ እስከ ጀሞ-3 ኮንዶሚኒየም የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ፈጣን መንገድ ኮሪደር ግንባታን በታህሳስ ወር ለማስጀመር መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
🛣 15.64 ኪሎ ሜትር ሽፋን፣ 20 ዘመናዊ ጣቢያዎችን እና 12 ተጨማሪ አገልግሎቶችን የሚይዘው ይህ ፕሮጀክት፤ በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር እያሱ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡
🚉 መንገዱ በቀን 400 ሺህ የሚደርሱ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚጠበቅ ሲሆን ወጪው በከተማ አስተዳደሩ እና በአጋር ድርጅቶች ይሸፈናል፡፡
#afromekina
Loading content...
