በአንዳንድ አካባቢዎች በ121 ብር ይሸጥ የነበረው ናፍጣ እስከ 200 ብር ደረሰ
መንግሥት የናፍጣ መሸጫ ዋጋ በሊትር 121 ብር ገደማ እንዲሸጥ ዉሳይ አስተላፎ እየገበረ ቢገኝም፣ በተለይ በሲዳማ ክልል ከሀገረ ሰላም ( ሐዋሳ) ዙሪያ ጨምሮ እስከ ዝዋይ ድረስ የአንድ ናፍጣ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ አሻቅቦ እስከ 200 ብር ድረስ በሕገወጥ መንገድ እየተሸጠ መሆኑን ካፒታል ጋዜጣ ባደረገው ምልከታ ለማወቅ ተችሏል።
ይህን ተከትሎ ናፍጣ ከህጋዊው ዋጋ አንፃር በ 79 ብር ልዩነት በአንዳንድ አካባቢዎች እስከ 65.29% ጭማሪ አሳይቷል።
ካፒታል እንደተመለከተዉ ፤ በሀገረ ሰላም ከተማ 30 ሊትር ናፍጣ በ165 ብር ዋጋ ሲሸጥ ጠቅላላ ዋጋው 4,950 ብር ሲደርስ፣ በዝዋይ ደግሞ 35 ሊትሩ በ185 ብር ዋጋ እስከ 6,475 ብር እየተሸጠ ሲሆን፣ በዚሁ ከተማ ( ዝዋይ) በሕገወጥ መንገድ ደግሞ በ200 ብር ዋጋ እስከ 7,000 ብር ድረስ በድብቅ እየተሸጠ ይገኛል።
በከተማዎቹ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በሚባልበት ደረጃ የመኪና ናፍጣን ጨምሮ ሌሎች የነዳጅ ምርቶች “የለም” እያሉ በመሆኑ፣ ምርቶቹን ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ሆኗል።
#afromekina
Loading content...
