አየር መንገዱ 120 አዳዲስ አውሮፕላኖችን አዘዘ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እያደገ የመጣውን የደንበኞች ቁጥርና የሥራ ስፋት ለማስተናገድ 120 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ማዘዙን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገለጹ።
ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ከጋዜጣ ፕላስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ በየጊዜው እያደገ በመምጣቱና የደንበኞች ቁጥርም እየጨመረ በመሆኑ ኦፕሬሽኑን ለመምራት አዳዲስ አውሮፕላኖች አስፈላጊ ሆነዋል።
በአሁኑ ጊዜ ወደ 120 የሚጠጉ አውሮፕላኖች ትዕዛዝ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ከታዘዙት ውስጥ ትናንሽ የሚባሉ አውሮፕላኖችን በእ.ኤ.አ ከ2026 ጀምሮ መረከብ እንደሚጀመር ገልጸዋል። ትላልቅ አውሮፕላኖችን ደግሞ ከ2028 ጀምሮ ባሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለመረከብ ታቅዷል።
በተጨማሪም በ2031 ርክክብ የሚደረግባቸውን አውሮፕላኖች ከአሁኑ ለማዘዝ ከቦይንግ፣ ኤርባስና ሌሎች ኩባንያዎች ጋር ድርድር እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
#afromekina
Loading content...
