በነዳጅ ቅሸባ የተጠረጠሩ 12 ማደያዎች ታገዱ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅርቦት ባለስልጣን በነዳጅ ማደያዎች የመቅጃ ማሽኖች (ዲስፔንሰሮች) ላይ ባደረገው ድንገተኛ ቁጥጥር፣ ትክክለኛውን ልኬት ባለማሳየት የነዳጅ ቅሸባ ሲፈጽሙ የተገኙ 12 ማደያዎችን አገደ።
ባለስልጣኑ ከግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ከተሞች ባካሄደው የቁጥጥር ዘመቻ የጥፋታቸውን ደረጃ በማረጋገጥ፣ ከሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ከአንድ እስከ ሁለት ወር የሚደርስ የነዳጅ ጭነት ዕገዳ ጥሏል።
በሌሎች ማደያዎች ላይ የተጀመረው ምርመራ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ የደረሰበትን የቁጥጥር ውጤት በቀጣዮቹ ቀናት ይፋ እንደሚያደርግ ባለስልጣኑ አስታውቋል።
#afromekina
Loading content...
