ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ
ታክሲዎች ይቀጣሉ
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ የህዝብ ማመለሽ ተሽከርካሪዎችን እንደሚቀጣ ገለጸ።
ቢሮው " ያለ ረዳት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች በከተማዋ እየበዙ ነው " ብሏል።
" ከዚህ በኋላ ግን ባለው መመሪያው መሰረት ረዳት የሌላቸውን ታክሲዎች እቀጣለሁ " ሲል አስጠንቅቋል።
ቢሮ " ያለ ረዳት ማሽከርከር ገንዘብ በመቀበል፣ ገቢና ወራጅ በመቆጣጠር የሹፌሩን ትኩረት ስለሚሰርቅ ለአደጋ ያጋልጣል " ብሏል።
" ከዚህ ቀደም ለሌሎች የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ብቻ ትኩረት በመስጠታችን ረዳት ያላቸውና የሌላቸውን ተሽከርካሬዎች የመለየት ውስንነት ታይቶብናል " ያለው ቢሮው " ከዚህ በኋላ ግን የታክሲ ረዳት መኖር አንዱ የትራፊክ ደህንነት አካል በመሆኑ ሁሉም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ ክትትል እናደርጋለን " ሲል ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።
#afromekina
Loading content...
