የከተማዋን መንገዶች ምቹና የተሳለጡ ለማድረግ የሚያስችሉ ከ110 በላይ የግንባታ ፕሮጀክቶች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ ነው
የከተማዋን የመንገድ ደኅንነት ለመጠበቅ ብሎም እንቅስቃሴን ምቹና የተሳለጠ ለማድረግ የሚያስችሉ 111 ልዩ ልዩ አዲስ እና የጥገና ግንባታ ሥራዎች በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ በዋናነት የከተማዋን የመንገድ መሠረተ-ልማት የመገንባት፣ የመጠገን እና የማሥተዳደር ኃላፊነት ወስዶ እየሠራ መሆኑን የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢያሱ ሰሎሞን ለኢዜአ ተናግረዋል።
በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት 111 ገደማ ልዩ ልዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ከእነዚህ መካከል 31 ያህሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች አዲስ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሁሉም ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 291 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍኑ የገለጹት አቶ ኢያሱ፤ ከ30 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ እንደሚደረግባቸው አረጋግጠዋል።
የከተማዋን የመንገድ ደኅንነት ለመጠበቅ ብሎም እንቅስቃሴን ምቹና የተሳለጠ ለማድረግ የመንገድ ጥገና ሥራዎች በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በአጠቃላይ እየተከናወነ ያለው የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ከማሳለጥ ባለፈ የጉዞ ጊዜን በመቀነስ ብሎም ነዳጅን በመቆጠብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
#afromekina #ኢዜአ
Loading content...
