የነዳጅ ዘይት ዋጋ ዛሬ በአማካይ 108 ዶላር ገብቷል።
ከጦርነቱ በፊት ከነበረዉ 40 በመቶ ጨምሯል።
እጥረቱና የዋጋ ንረቱ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ቻድ፣ ማላዊ፣ ጋቦን፣ ታንዛኒያን በመሳሰሉ ሐገራት የትራንስፖርት አገልግሎት አንድም እንዲቋረጥ ሁለትም በእጥፍ እንዲጨምር አድርጎታል።
የተለያዩ ሐገራት ለጄኔሬተር የሚያዉሉት ነዳጅ በማጣታቸዉም የመብራት አገልግሎት ለማቋረጥ ተገድደዋል።
ኢራን በሆርሙስ ወሽመጥ በኩል የሚቀዝፉ የእስራኤል፣ የዩናይትድ ስቴትስና የተባባሪዎቻቸዉን ሐገራት መርከቦች እንደምትመታ በመዛትዋና በመምታቷም ጭምር በብዙ መቶ የሚቆጠሩ መርከቦች ከወሽመጡ ግራ ቀኝ ለመቆም ተገድደዋል።
የኢራን እገዳ ለመስበር የተለያዩ ሐገራት የጦር መርከብ እንዲያዘምቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ያቀረቡትን ጥያቄ ብዙ መንግሥታት አልተቀበሉትም።
የሩሲያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀዉ ደግሞ የሆርሙስ ወሽመጥ ዳግም አገልግሎት መስጠት የሚችለዉ በድርድር ብቻ ነዉ እንደ DW ዘገባ ።
#afromekina
Loading content...
