በውሃ ላይ የሚያርፉ አውሮፕላኖች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ነው
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለቱሪዝም አገልግሎት የሚውሉና በውሃ ላይ ማረፍ የሚችሉ አውሮፕላኖችን በቀጣይ ጥቂት ወራት ወደ ሀገር ውስጥ ሊያስገባ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለፁት፤ አየር መንገዱ የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግና በቂ የአውሮፕላን ማረፊያ በሌላቸው የቱሪስት መዳረሻዎች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ በውሃ ላይ የሚያርፉ አውሮፕላኖችን በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባል።
አውሮፕላኖቹ በመጋቢትና ሰኔ ወራት ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገቡና የሙከራ አገልግሎት እንደሚጀምሩም ገልጸዋል።
እነዚህ አውሮፕላኖች በውሃም ሆነ በመሬት ላይ ማረፍ የሚችሉ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በቅርቡ የሚጀመረው የሙከራ አገልግሎት ስኬታማ ከሆነ ተጨማሪ አውሮፕላኖች እንደሚታዘዙ አስረድተዋል።
ይህም ወደ ቱሪዝም መዳረሻዎች በአውሮፕላን ለመጓዝ ለሚፈልጉ መንገደኞች ትልቅ አማራጭ እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
#afromekina
Loading content...
