ፓኪስታን በነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት ጥብቅ የቁጠባ እርምጃዎችን አወጀች
በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ግጭት ሳቢያ የዓለም የነዳጅ ዋጋ አንድ በርሜል 100 ዶላር በማለፉ፣ ፓኪስታን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቁጠባ መመሪያዎችን አስተላለፈች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሻሪፍ ሰኞ ዕለት ባደረጉት ንግግር፣ ትምህርት ቤቶች ለሁለት ሳምንታት እንዲዘጉና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ በይነ-መረብ ትምህርት እንዲቀይሩ አዝዘዋል።
በተጨማሪም የመንግስትና የግል ሴክተር ሰራተኞች በግማሽ ቀን እንዲቀንሱ፣ ቀሪዎቹም ከቤታቸው እንዲሰሩ ተወስኗል።
የመንግስት ባለስልጣናት አዳዲስ የቢሮ እቃዎችን እንዳይገዙና ከአስቸኳይ ከደህንነት ጉዳዮች ውጭ ወደ ውጭ ሀገር እንዳይጓዙ ታግዷል።
ይህም የሆነው ሀገሪቱ ለግብርና እና ለትራንስፖርት ዘርፍ የምትጠቀመው ነዳጅ በከፍተኛ ሁኔታ በመወደዱ ወጪን ለመቀነስ ታስቦ ነው።
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
