የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሁመራ የሚያደርገውን በረራ ዳግም ጀመረ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለዓመታት ተቋርጦ የነበረውን ወደ ሁመራ አየር ማረፊያ የሚያደርገው በረራ ዛሬ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ዳግም መጀመሩ ተገለጸ።
በረራው የተጀመረው ባሳለፍነው ውር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሁመራ በረራ እንድሚጀምር በይፋ ማስታወቁን ተከትሎ ነው።
በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ወደ ሁመራ አየር ማረፊያ መደበኛ መረራ መጀመሩን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የበረራው መጀመር ኢንቨስትመንት በማነቃቃት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
በተጨማሪም፣ በረራው በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስተጋብሮች ላይ ያለው አስተዋፅዖ ጎላ ያለ መሆኑን ተጠቁሟል።
#afromekina
Loading content...
