ለሶስት ወር ከነዳጅ ጭነት ትስስር እገዳ ተጥሎበታል" - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን
ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጥቶበት ወደ አገር የሚገባን ነዳጅ ኃላፊነት በተሞላው መንግድ ለህዝብ ጥቅም ማዋል ሲገባው ያለአግባብ እንዲፈስ ያደረገ ማደያ ለሶስት ወር ከነዳጅ ጭነት ትስስር እገዳ ተጥሎበታል።
በአሪሲ ዞን ዳክሲሰ በሚባል ቦታ ሥራ የጀመረ ግሎባል የሚባል ማደያ ከነዳጅ መቅጃ ማሽን ነዳጅን ሲያርከፈክፍ በማህበራዊ ትስስር ገፆች መታየቱን ተከትሎ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ጉዳዩን ማጣራቱን ገልጿል።
በዚህም ባለሥልጣኑ ድርጊቱን መፈጸሙን በማረጋገጡ ይህን ድርጊት የፈጸመው ማደያ በነዳጅ ግብይት አዋጅ ቁጥር 1363/2017 አንቀጽ 7(10)ስር ያለዉን ግዴታ በመጣስ በአንቀጽ 11(9)መሠረት ህገ ወጥ ድርጊት ፈጽሞ ስለተገኘ የወንጀል ተጠያቂነቱ የሚቀጥል ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 23(1)መሠረት ለ3ወራት ፈቃዱ እግድ አስተላልፎበታል፡፡
#afromekina
Loading content...
