ወደሀገር መግባት የሚችሉ ተሽከርካሪዎችን የሚለይ መመሪያ ተዘጋጀ
በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ናቸው ወደ ሀገር ቤት መግባት ያለባቸው? የሚለውን የሚወስን መመሪያ ተዘጋጅቷል፤ በቅርቡም ይፀድቃል ሲል የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
በላይአብ ሞተርስ እና የቻይናው ዩቺ አይ ኩባንያ በተፈጥሮ_ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት መስማማታቸውም ተሰምቷል፡፡
አሁን የተለያዩ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣት ላይ የሚገኘው በላይ አብ ሞተርስ ከዶንግ ፊንግ ሞተርስ ጋር በመሆን በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለማቅረብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ተናግሯል፡፡
የመኪናዎቹ ሽያጭ ወደ ገበያ በሚገባበት ወቅት አስፈላጊውን የመኪና መለዋወጫና ሌሎች ግብአቶችን ለማቅረብ ከስምምነት መድረሱንም ሰምተናል፡፡
#afromekina
Loading content...
