ዘለንስኪ ድሩዝባ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመርን እንዳያጠቁ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
የሃንጋሪ የፖለቲካ ተንታኝ ዞልታን ኮስኮቪች በመላው ዩክሬን ውስጥ ከተሰተው መጠነ-ሰፊ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በኋላ በኤክስ ገጻቸው እንደፃፉት፣ "ከሃንጋሪ የበለጠ ኤሌክትሪክ እንደሚያስገቡ የሆነ ነገር ሹክ ብሎኛል። የድሩዝባ ማስተላለፊያ ደኅንነቱ ቢጠበቅ ይሻላል" ሲሉ አሳስበዋል።
በሃንጋሪና በዩክሬን መካከል ያለው ግጭት የድሩዝባ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ተባብሷል።
የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ሲያርቶ፣ ዩክሬን አገራቸውን ማስፈራራትና ለሃንጋሪ የኃይል አቅርቦት ወሳኝ በሆኑ መሠረተ ልማቶች ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት እንድታቆም ማሳሰባቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
#afromekina
