በነጭ ናፍጣ ብቻ በሊትር 10 የዋጋ ብር ጭማሪ ተደርጎ 139.84 ብር ገብቷል።
ቤንዚንም የ3 ብር ጭማሪ ተደርጎ በሊትር 132.18 ብር ሆኗል።
በመጋቢት 2018 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን ማደያዎች ገለጹ።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ደብዳቤ፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ከመጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን ያስረዳል።
በደብዳቤው በተገለጸው መሰረት በሊትር፦
-ቤንዚን 132.18 ብር
-ኬሮሲን 146.14 ብር
-ነጭ ናፍጣ 139.84 ብር
-ቀላል ጥቁር ናፍጣ 137.03 ብር
-ከባድ ጥቁር ናፍጣ 133.45 ብር
-የአውሮፕላን ነዳጅ 145.23 ብር ሆኗል።
በዚህም ነጭ ናፍጣ ላይ የ10 ብር፣ ኬሮሲን ላይ የ7 ብር፣ ቤንዚን ላይ የ3 ብር፣ በየካቲት ወር በሊትር ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ በየካቲት 2018 ዓ/ም ቤንዚን 129.12 ብር፣ ነጭ ናፍጣ 129.12 ብር፣ ኬሮሲን 129.12 ብር ይሸጥ ሲሸጡ ነበር።
በአማኑኤል አክሎግ
#afromekina
Loading content...
